Love letter in note verbale

መለያ ቁጥር: አፍቀ144/14

ግንቦት 10 ቀን 2007 ዓ.ም.

አፍቃሪ አዲስ አለም ደስታ ለተፈቃሪት ጲኒኤል ያለዉን ፍቕር ሲገልፅ ክብር ይሰማዋል፡፡  እንዲሁም ለተፈቃሪው እራት የመጋበዝ ሀሳብ እንዳለው በዚህ አጋጣሚ ማሳወቅ ይፈልጋል፡፡ የሚመረጡ ቀናትም ግንቦት 15 እና 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ማለትም ቅዳሜ እና እሁድ መሆናቸዉን ሲያሳዉቅ ክብር ይሰማዋል፡፡

አፍቃሪው ከተፈቃሪዉ በሁለትዮሽ የግል ጉዳይ ለመወያየት እንዲሁም ስለተፈቃሪ የፍቅር ሁኔታ፣ የሚወዱትንና የሚጠሉትን፣ ስላሳለፉት ሂወት፣ ስለቤተሰባቸው ሁኔታ፣ እና ስለቀጣይ የሂወት እቅዳቸው ለመወያየት ጥሪዉን ያቀርባል፡፡

አፍቃሪው ለጠየቃቸው ጥያቄዎች ተፈቃሪው ለሚሰጠው ፈጣን መልስ አመስጋኝ ነው፡፡

አፍቃሪው ለተፈቃሪው ያለዉን ከፍተኛ ፍቅር  እየገለፀ በዚህ አጋጣሚ ለተፈቃሪ ያለዉን ከፍተኛ የአክብሮት ማረጋገጫ ማደስ ይፈልጋል፡፡

አፍቃሪው

ተፈቃሪው

ልብ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s