“የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ” የሚባል “ፍጥረት” ግን አያስፈራም?

የፍትሕና የሕግ ምርምር ኢንስቲትዩትና የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ተጠሪነት በቅርቡ ይቋቋማል ተብሎ ለሚጠበቀው የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እንዲዘዋወር የሚያደርጉ የሚቋቋመው ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በሕግ ጉዳዮች የፌዴራል መንግሥት ዋና አማካሪና ተወካይ ሆኖ እንደሚሠራ ረቂቅ አዋጁ ይገልጻል፡፡ ፓርላማው ማሻሻያውን ካፀደቀው ፍትሕ ሚኒስቴር እንደሚፈርስ፤ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በሙስና የተጠረጠሩ ግለሰቦችን የመክሰስ ሥልጣኑ ተቀንሶ፣ መልካም ሥነ ምግባርን በማስረፅ ተግባር ላይ ብቻ እንዲያተኩር ይገደዳል፡፡ የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተቋም ተጠሪነትም ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እንደሚሆን፣ የፌዴራል ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በፓርላማው እንደሚሾም ረቂቁ ይገልጻል፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሕግ ማስከበር ተግባር በዓቃቤ ሕግ የሚከናወን መሆኑን፣ ነገር ግን ይህ የዓቃቤ ሕግነት ሥራ በተለያዩ ተቋማት ተበታትኖ እየተሠራ የሚገኝ በመሆኑ የሕግ ማስከበር ሥራውን ውጤታማና ቀልጣፋ እንዳይሆን ማድረጉን ይገልጻል፡፡ እስካሁን ባለው አፈጻጸም የዓቃቤ ሕግነት ሥራ በተለያዩ የፌዴራል ተቋማት ማለትም በፍትሕ ሚኒስቴር፣ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን፣ በሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ እንዲሁም በንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ተበትኖ የሚገኝ መሆኑን ያስረዳል፡፡
የወንጀል ምርመራ እንዲጀመር ፌዴራል ፖሊስን ማዘዝ፣ የተጀመረ የወንጀል ምርመራ ላይ የክትትል ሪፖርት እንዲቀርብ፣ እንዲሁም ምርመራው በአግባቡ ተከናውኖ እንዲጠናቀቅ፣ በሕዝብ ጥቅም መነሻ ወይም በወንጀል የማያስጠይቅ ሁኔታ መኖሩ በግልጽ ሲታወቅ እንዲቋረጥ፣ ወይም የተቋረጠው እንዲቀጥል የሚያደርግ መሆኑን ረቂቁ ያስረዳል፡፡
ፖሊስ በራሱ የጀመረው ምርመራ ካለ ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የማሳወቅ ግዴታ ሲኖርበት፣ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በበኩሉ በምርመራ መዝገብ ላይ የሰጠውን ውሳኔ ወይም ፍርድ ቤት በመዝገቡ ላይ ስለተሰጠው ውሳኔ ለፖሊስ እንደሚያሳውቅ ረቂቁ ይገልጻል፡፡ ምርመራ የማድረግ፣ ማስረጃ የማሰባሰብ፣ ኤግዚቢት የመያዝ፣ ተጠርጣሪን የማቅረብና የመሳሰሉት ተግባራት የፖሊስ መሆናቸውን የረቂቁ ማብራሪያ ያስረዳል፡፡ ዓቃቤ ሕግ ደግሞ ምርመራውን የመምራት ሥልጣን እንደሚኖረው፣ በተጨማሪም የማኅበረሰብ አገልግሎት ቅጣቶችን የሚያስፈጽም አደረጃጀትን ማመቻቸት፣ ፍርድ ቤቶች በወንጀል ጉዳይ የሚሰጧቸው ውሳኔዎችና ትዕዛዞች መፈጸምና መከበራቸውን መከታተል፣ ሳይፈጸሙ ከቀሩ ወይም አፈጻጸማቸው ሕግን ያልተከተለ ከሆነ ጉዳዩን ላየው ፍርድ ቤት በማመልከት የእርምት ዕርምጃ እንዲወሰድ የማድረግ ኃላፊነት እንደሚኖረው በረቂቅ አዋጁ ተገልጿል፡፡
የኔ ጥያቄ፣ ይሄ ሁሉ ስልጣን ከተሰጠው ከማንኛውም መሥሪያ ቤት የበለጠ ስልጣን ይኖሯል። With great power comes….

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s