በፖለቲካ ኢኮኖሚ ትንታኔ ማዕቀፍ፣ ኢኮኖሚው ከፖለቲካ፣ ማሕበራዊ እና ሌሎች ጉዳዮች ለይቶ ማየት ከባድ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት፣ እንዲሁም በአመዛኙ በፖለቲካ ዘርፉ ብዙ ዓቅም እና ክህሎት ያላቸው ባለሞያዎች በብቃት መረጃ በማድረስ የሕበረተሰቡ በጉዳዮቹ ላይ ያለውን አረዳድ በማስፋት ዓይነተኛ ሚና እየተወጡ ይገኛሉ።
እኔም በበኩሌ የኢኮኖሚ ዘረፍ ያሉበትን ክፍተቶች በሚገባው መጠን ትኩረት ያገኙ ዘንድ የኢኮኖሚ ሁኔታው፣ ያሉበትን መዋቅራዊ ክፍተቶች እና ይጠቅማሉ ብዬ የማስባቸው ምክረ ሃሳቦች ግዜ እና ዓቅም በፈቀደው መጠን በማቅረብ ኣስተዋፀኦ ማድረግ ተገቢ መሆኑን በማመን በቀጣይነት በአጭሩ ለማቅረብ ጥረት አደርጋለሁ።
ገንቢ አስተያየታችሁም ይጠበቃል።
